በሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት የጽሕፈት መሳሪያ፣ የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ህትመት፣ የእርሻ መገልገያ፣ ሸድኔት፣ የመኪናና የሞተር ብስክሌት መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማና ባትሪ ግዥ በ9 ሎት ያወጣው ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ።
የቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ ቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ ሎት2 የጽዳትዕቃዎች ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት4 የህትመት ስራዎችሎት 5 የእርሻ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት6 ሸድኔት፣ሎት7 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፤ሎት8 የሞተር ብስክሌት መለዋወጫ እቃዎች ሎት 9 የመኪና ጎማና ባትሪ እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1-15 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልታችሁ መወዳደር የምትችሉና በምትወዳደሩበት እቃ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባችሁ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግዥ መጠን ከብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ከሚሞሉት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሞሉት ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ኦርጅናሉን ወይም ለመ/ቤቱ ገ/ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ15/03 /2019 ዓ.ም ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት ተከታታይ ቀን ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ታሽጎ 3:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የተጠቀሰው የመጨረሻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ይተላለፋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን፣ በኦርጂናልና በኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው አቅራቢ ስለትክክለኛ የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በጨረታው አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ /CPO/ በማስያዝ ውል መፈረም አለበት።
- መ/ቤቱ ከሚገዛቸው እቃዎች ብዛት ላይ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው።
- አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች ቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት የመጫኛና የማውረጃ የጉልበት ዋጋ በመሸፈን ማስረከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- በጨረታ ግምገማ ውጤት ቅር የተሰኘ ተጫራች ውጤቱ በተገለፀበት በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ጨረታውን ላወጣው ግዥ ፈፃሚ አካል በፅሁፍ ማቅረብ ይችላል።
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፤
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የዕቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ድምር ስለሆነ የሁሉም ዕቃ ዋጋዎች መሞላት አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- የተሳሳተ/ስርዝ ድልዝ/የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል በህግም ያስቀጣል
- ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ 033-334-0331/332 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ 3% እና 15% ተቀናናሽ ግብር ሰብሳቢ መሆኑ ይታወቅ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቆቦጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽ/ቤት
Summary
Kobo Girana Valley Development Program Office (North Wollo, Amhara) buys goods in 9 lots: stationery, cleaning items, electronics, printing, farm tools, shade net, vehicle and motorcycle spare parts, and vehicle tyres and batteries.
