Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline24 Dec 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 25% CPO በአማራ ባንክ ስም
  • opening dateንብረት 1 ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ፣ ንብረት 2 ወሊዮ ቅርንጫፍ
  • Sector Foreclosure , House and Building , House and Building Maintenance , Sales

አማራ ባንክ አ.ማ በጎንደር ከተማ የሚገኝ G+3 የንግድ ህንፃ እና በወልዲያ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በመያዣ የተረከባቸውን 2 ንብረቶች ለመሸጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ (ቁጥር አማራ ባንክ/63/2019)።

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር አማራ ባንክ/63/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍከተማክ/ከተማወረዳቀበሌየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ቀንሰዓትቦታ
1አቶ አራጋ ተድላሁን ታገለአቶ ግርማ ስዩም አዉስማሀኢልጎንደርጎንደርማራኪ-18200 ካ.ሜ20458/14G+3 ለንግድ አገልግሎት14,389,688.52ታህሳስ 15 ቀን 2019 ዓ.ምከ 3:00 እስከ 4:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ(ጎንደር)
2አብርሃም አብዲሳ አበበአብርሃም አብዲሳ አበበወሊዮወልዲያ-ወልዲያ-200M²W/518/93ለመኖሪያ1,452,805.97ታህሳስ 16 ቀን 2019 ዓ.ምከ4:00 እስከ 5:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ወሊዮ ቅርንጫፍ ቢሮ

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፣ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚያመጣው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል።
  4. የሐራጅ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝ ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል።
  5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ) ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርክአውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል።
  8. ጨረታው በሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ፤ - ተጫራቾች መያዣ ለሚያቀርቡት እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል። - በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑት ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል። - በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው።
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
  12. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል።

አማራ ባንክ አ.ማህበር

Summary
Amhara Bank S.C. auctions two foreclosed properties (first auction): a G+3 commercial building on 200 sq.m in Maraki, Gondar, and a 200 sq.m residential house in Woldia. The bank may finance qualified winners up to 100%.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender