የደቡብ ክልል ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን ያገለገለ የጭነት ተሽከርካሪ ሽያጭ
የደቡብ ክልል ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን
የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ/001/2019
የደቡብ ክልል ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን ኤፍ ኤስ አር/FSR/ 2012 ሞዴል የጭነት ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ስለዚህ ማንኛውም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች:-
- የተሽከርካሪውን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ::
- የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ተሽከርካሪውን ከተ.እ.ታ በፊት የሚገዛበትን ዋጋ 1/10ኛውን ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት በባንክ ክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1,000/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ በመቅረብ መግዛት ይቻላል::
- የዋጋ ማቅረቢያ እና ሌሎች መረጃዎችን የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከረፋዱ 5:00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ የሚከፈት ይሆናል:: 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይፈፀማል::
- በንብረቱ ላይ ከመንግስት የሚፈለጉ ግብሮች፣ ቫት፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎች በጨረታው አሸናፊ ይሸፈናሉ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ ሀዋሳ ከተማ ሞሀ የለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0935979146/0912142464/0911761329 ደውሉ መጠየቅ ይችሳሉ::
የደቡብ ክልል ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌደሬሽን
Summary
Southern Region Farmers Cooperative Federation is selling an FSR model cargo truck as-is by sealed bid; the truck can be inspected at its Hawassa office.
