Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት
  • Address አዳማ ከተማ ናፍራን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-212-04-17
  • Website
  • Deadline29 Dec 2026, 10:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4ኛ ሲ.ፒ.ኦ
  • opening dateታህሳስ 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:30-6:30፣ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ (አሰላ)
  • Sector Land , House, Building And Warehouse , Business, Industry And Factory Foreclosure

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት በአሰላ ከተማ ቀበሌ 10 በ876 ካሜ² ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ ዲጂታል የልብስ ስፌት ማሽኖች፣ ጥሬ ዕቃዎችና የቢሮ ዕቃዎችን በመነሻ ዋጋ ብር 61,041,737.69 ለመሸጥ ያወጣው 2ኛ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ለወ/ሮ አመቤት ስዩም ለሰጠው ብድር አመላለስ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን ንብረቶች በዐዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው ዐዋጅ ቁጥር 216/92 እንዲሁም በዐዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው/ ስምየሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታየሐራጁ መነሻ ዋጋየሐራጁ ደረጃሐራጅ የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት
ወ/ሮ አመቤት ስዩም አለሙበኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ቀበሌ 10 (ወልኪሳ) ውስጥ በ876 ካሜ² ይዞታ ላይ ያረፉ ግንባታዎች፣ዲጂታል የልብስ ስፌት ማሽኖች ጥሬ ዕቃዎችና ያለቀለት የጨርቅ ውጤቶች እና የቢሮ ዕቃዎችና ቁሶች61,041,737.692ኛበድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታህሳስ 20ቀን 2019 ዓ.ም ከ4:30-6:30

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የሐራጁን የመነሻ ዋጋ 1/4ኛ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ለባንኩ በማስያዝ በእለቱ እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ በመመዝገብ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል።
  3. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል።
  4. የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው የፕሮጀክቱ ንብረቶች ካሉ ገዢው የቀረጥ ነፃ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
  5. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከገዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. የጨረታው አሸናፊ 15 ፐርሰንት የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ጨምሮ ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
  7. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች/ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው /ተበዳሪ ወኪል እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ተወካዮች ብቻ ናቸው።
  8. ከፕሮጀክቱ ጠቅላላ ይዞታ 1.8 ሜትር ለኮሪደር ልማት በአሰላ ከተማ መስተዳደር የሚቀነስ መሆኑ እና ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር-022-211-66-87 ላይ መደወል ይችላሉ።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሐራጅ አይገደድም።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማ ዲስትሪክት

Summary
Development Bank of Ethiopia, Adama District, holds a 2nd foreclosure auction of a garment project in Asella Kebele 10: buildings on an 876 sq.m plot, digital sewing machines, raw materials, finished textiles and office items. Partial bank financing is available.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender