የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ ገንደቦል ቡልጎ ቀበሌ 11,342.36 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈውን የዳሺዮንግ ማኑፋክቸሪንግ የቀለም ፋብሪካ ከነሙሉ ንብረቱ በመነሻ ዋጋ ብር 27,548,162.07 ለመሸጥ ያወጣው ድጋሚ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ብሩክ ቱርጋ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ዳሺዮንግ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.22026 በ30/06/2018ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.24141 በቀን 28/08/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ባለዕዳ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ዳሺዮንግ ማኑፋክቸሪንግ የቀለም ፋብሪካ የሚገኝበት አድራሻ በደብረብርሃን ከተማ ልዩ ቦታው ገንደቦል ቡልጎ ቀበሌ የካርታ ቁጥር 1804 የቦታ ስፋት 11,342.36 ካ/ሜ (1.13 ሄ/ር) ሎት ያረፈ የቀለም ፋብሪካ ከነሙሉ ንብረቶቹ የሐራጅ መነሻ 27,548,162.07 (ሃያ ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ከ07/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 27 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.24141 በቀን 30/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 6,887,040.51 (ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማንያ ሰባት ሺህ አርባ ብር ከ51/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 1 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡ ፡የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤ/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን ፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ቤት ም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
