Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት
  • Address ባህርዳር, Phone: 058-226-27-40
  • Website
  • Deadline22 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየሚገዙበት ዋጋ 25% በCPO
  • opening dateታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ/ም ሐራጅ፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት ጽ/ቤት
  • Sector Generators , Business, Industry And Factory Foreclosure , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ያስረከባቸውን ሁለት የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኖች፣ አንድ ጀነሬተርና 346 ሲሊንደሮችን በባህርዳር ከተማ ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የመጀመሪያ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለበረንታ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰጠው ሁለት የኦክስጅን ማምረቻ ማሽነሪዎች ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሰረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየንብረት ዓይነትየሚገኝበት አድራሻብዛትየመነሻ ዋጋቦታቀንሰዓት
1የሚሰሩ ሁለት የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኖች (50m³/hr እና 80 m³/hr) የማምረት አቅም ያላቸው፣ አንድ ጀነሬተር(ከATS ጋር Prime Power 280 Kw የሆነ) እንዲሁም 346 ሲሊንደሮችባህርዳር ከተማ ቀበሌ 142(ኦክስጅን ማሽን) 1(ጀነሬተር)33,040,292.78የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት ጽ/ቤትታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ/ም4:00-6:00

የሽያጭ መመሪያ:-

  • ንብረቶቹን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ የሚገዛበትን ዋጋ 25% በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዲስትሪክቱ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ መደራደር ይችላል።
  • የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኖቹ እና ጀኔሬተሩ ቀድሞ ከተተከለበት ቦታ ተነቅሎ በባንኩ መጋዘን ውስጥ የተቀመጡ ናቸው።
  • የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል።
  • ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ ክፍያን ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
  • አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ካሟላ ሽያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል።
  • አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ አጠቃሎ መክፈል አለበት። ካልከፈለ ባንኩ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሽያጩ በድጋሚ ይካሄዳል።
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ/መንገድ ካገኘ ሽያጩን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:- 058-226-27-40

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባህርዳር ዲስትሪክት

Summary
Development Bank of Ethiopia Bahir Dar District auctions repossessed lease-financed equipment: two working oxygen production machines (50 and 80 m3/hr), a 280 kW generator with ATS and 346 cylinders, held in Bahir Dar. Open to any buyer; lease financing possible.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender