አማራ ባንክ አ.ማ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 02 የሚገኘውን 10,000 ካ.ሜ ይዞታ ያለውን የአቶ ምህረት ፈረደ ታረቀኝ የፋብሪካ ህንፃና ማሽነሪ በመነሻ ዋጋ ብር 66,906,319.84 ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ (ቁጥር አማራ ባንክ/61/2019)።
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ/61/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/ አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ | ቀን | ሰዓት | ቦታ |
|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|---|
| 1 | አቶ ምህረት ፈረደ ታረቀኝ | አቶ ምህረት ፈረደ ታረቀኝ | እንጅባራ | እንጅባራ | - | - | 02 | 10,000 ካ.ሜ | 05/08 | የፋብሪካ ህንፃ ከነዝቃይ መሳሪያዎችና ማሽን | 66,906,319.84 | ታህሳስ 13 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓት | አማራ ባንክ አ.ማ ባህር ዳር ዲስትሪክት(ባ/ዳር) |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው።
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም። ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚያመጣው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል።
- የሐራጅ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝ ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/ አሸናፊው/ ይከፍላል።
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል። ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ) ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርክዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል።
- ጨረታው በሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል።
- ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ፤ - ተጫራቾች መያዣ ለሚያቀርቡት እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል። - በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑት ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል። - በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል።
- ለበለጠ መብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅቶችም ያገለግላል።
አማራ ባንክ አ.ማህበር
Summary
Amhara Bank S.C. auctions a foreclosed factory building with its fixed machinery on a 10,000 sq.m plot in Kebele 02, Injibara town (first auction). The bank may finance qualified winners. Viewing by appointment with the Workout and Recovery unit.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
