የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለመንገድ ጥገና ስራ የሮሎ ማሽን፣ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪናና ኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ በ2 ሎት ያወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው ለመንገድ ጥገና ስራ አገ/ት የሚውል
- ሎት 1፡- የሩሎ ማሽን እና ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና
- ሎት 2፡- የኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በማሽነሪ ኪራይ የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ አንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 2000/ሁለት ሺ ብር/ ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ በሁለት ፖስታ በማድረግ እና በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ እና ለሎት ሁለት 200,000/ሁለት መቶ ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3:00 ሁለቱም ታሽጎ በዚያው ቀን ሎት አንድ በ4:00 ሠዓት ላይ ሎት ሁለት 8:30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው።
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Summary
Mizan Aman City Finance Office (South West Ethiopia) rents machinery for road maintenance in 2 lots: a roller and Sinotruk dump trucks, and an excavator. Licensed machinery rental firms with VAT, TIN, tax clearance and supplier registration may bid.
