Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጫታ ከተማ መስተዳድር ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0925752474
  • Website
  • Deadline07 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1500(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:30
  • Sector Road And Bridge Construction , Machinery Rental

የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጫታ ከተማ መስተዳድር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የሚውሉ ግሬደርና ዶዘር D7R ማሽነሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ያወጣው ማስታወቂያ።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጫታ ከተማ መስተዳድር ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለመንገድ ስራ የሚሆኑ ማሽነሪ ክራይ (Machinory Lease) ዓቅርቦት ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጫታ ከተማ መስተዳድር ገንዘብ ጽ/ቤት በመቻራ ሚጫታ ከተማ ማስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት ባጀት በመቻራ-ሚጫታ ከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ማሽነሪ ክራይ ስለሚፈልግ ለዚህም ስራ የሚውሉ ማሽነሪዎችን:-

  1. GRADER ለ250 ሰዓት ነዳጅን ችለው(ጨምሮ)
  2. Dozer D7R ለ400 ሰዓት ነዳጅን ችለው(ጨምሮ)

ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን /ማህበራት/ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ የማሽነሪ አቅርቦት ፍቃድ ያላችሁ ድርጅቶች /ማህበራት/ እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።

  1. ተወዳዳሪዎች የታደሰ ንግድ ፍቃድና የዚህን ዓመት /የ2019/ ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ተወዳዳሪዎች በማሽነሪ ዓቅርቦት ፍቃድ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተወዳዳሪዎች የ50,000 /የሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሠነድ የማይመለስ 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመቻራ ሚጫታ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፣
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት /15/ የስራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፣
  7. ተወዳዳሪዎች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦሪጂናሉንና አንዱን ኮፒ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት /15/ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
  8. ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሠነዱን በጥንቃቄ እንዲሞሉ እያሳሰብን በየትኛውም መልኩ ስርዝና ድልዝ ተቀባይነት የለውም፣ ወይም ከፊትለፊት የተፈረመ መሆን ይኖርበታል፣
  9. ጨረታው በ16ኛው /በአስራ ስድስተኛው/ ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፣
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው በተባለው ሰዓት ይከፈታል፣
  11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአጋጣሚ ከስራ ቀን ውጪ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  13. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፉበት ዋጋ ላይ 10% የሚሆን ብር (performance bond) ለማስያዝ ፍላጎት ያለው መሆን አለበት።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን የመቻራ ሚጫታ ከተማ መስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Summary
Mechara Michata Town Finance Office (East Oromia Zone) rents a grader for 250 hours and a D7R dozer for 400 hours, fuel included, for internal town road works. Licensed machinery rental firms with VAT and paid taxes may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender