የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በሮድ ፈንድ የሚሰሩ የኮብልስቶን ንጣፍ (3 ሎት)፣ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ (2 ሎት) እና የጠጠር መንገድ (1 ሎት) ስራዎችን ለማሰራት GC-5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን የጋበዘበት ግልጽ ጨረታ (HCA/RF/CW-01 እስከ 06/2019)።
Hawassa City Administration
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በሮድ ፈንድ ለሚያሰራው የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ 3 (ሶስት) ሎት የጨረታ መለያ ቁጥር HCA/RF/CW-01/2019, HCA/RF/CW-02/2019, HCA/RF/CW-03/2019፣ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ 2 (ሁለት) ሎት የጨረታ መለያ ቁጥር HCA/RF/CW-04/2019, HCA/RF/CW-05/2019 እና የጠጠር መንገድ 1 (አንድ) ሎት የጨረታ ቁጥር HCA/RF/CW-06/2019 ዓ/ም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ተቋራጭ መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ GC-5 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፣
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የግብር ግዴታ የተወጡበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
- የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ፣ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ለሃያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በባንክ አካውንት በመክፈል፣ መጫረቻ ሰነዱን ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 ግዢ ኬዝ ቲም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ21ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4:30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከአንድ ፕሮጀክት በላይ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ5% (ከአምስት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሰንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከሃያ እስከ ሰላሳ ፐርሰንት (20% እስከ 30%) በታች ከሆነ በተሰበረው ተብለው ተይዞ ከተጫራቹ ማብራሪያ ተጠይቆ ተቀባይነት ካገኘ የሚያልፍ ይሆናል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጣረስ ሁኔታ ካለ፣ የጨረታ ሰነዱ በላይነት ይኖረዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
ሀዋሳ
Summary
Hawassa City Administration Finance and Economic Development Department invites GC-5 and above contractors for Road Fund works: cobblestone paving (3 lots), flood drainage ditch construction (2 lots) and a gravel road (1 lot) in Hawassa.
