የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የጎርፍ መውረጃ ዲች፣ የመኪና መሸጋገሪያ ጥገና፣ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ግንባታና የጠጠር መንገድ ጥገና ስራዎችን በ3 ሎት ለGC-5/RC-5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችና ለኮብል ንጣፍ ማህበራት ያወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በሮድ ፈንድ በጀት የሚ/አ/ከ/ዋና ማዘጋጃ ቤት በባለቤትነት ለሚያሰራው
- ሎት 1 የጎርፍ መውረጃ ዲች ቦይ እና የመኪና መሸጋገሪያ ጥገና ስራ
- ሎት 2 የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድ ግንባታ ስራ
- ሎት 3 የጠጠር መንገድ ጥገና
ለሎት አንድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ አምስት/GC-5 እና ከዚያ በላይ ሎት ሁለት የኮብል ንጣፍ ማህበር እና ሎት ሶስት ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና የመንገድ ስራ ተቋራጭ ደረጃ አምስት/ GC/RC-5/ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
- ተራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ አንላይን የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ኬዝ ቲም የሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን ብር 2000/ሁለት ሺ ብር/ ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ እና ለሎት ሁለት 70,000/ሰባ ሺ ብር/ ለሎት ሶስት 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ5:00 ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ሎት አንድ 3:30፣ ሎት ሁለት 5:00 እና ሎት ሶስት 9:00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Summary
Mizan Aman City Finance Office (South West Ethiopia) tenders Road Fund works in 3 lots: flood drainage ditch and vehicle crossing repair (GC-5+), cobblestone road construction (cobble associations) and gravel road maintenance (GC/RC-5+).
