የመካከለኛ ኦሮሚያ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የከተማውን ኮሪደር ልማት ስራ ለማሰራት የኮንስትራክሽን G-3 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን የጋበዘበት በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ።
የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የመካከለኛ ኦሮሚያ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የከተማችን ኮሪደር ለማሠራት የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ።
ሀ የተወዳደሪዎች መመሪያ
- በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2018/2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ ተሰማርተው ለመገኘታቸው ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ በሙያው G-3 እና ከዚያ በላይ ያለቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን በሥራ ሰዓት እስከ 6:30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 5000 ( አምስት ሺ ብር ) በሲንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1055210501213 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣትና ከገቢዎች በማወራረድ ከገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት በ22ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000/ አራት መቶ ሽህ ብር/ ወይም ሲፒኦ በማስያዝ ለጊዜው በተዘጋጀው ሣጥን ያስገባሉ።
- ሰዓቱን አሳልፎ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው በ22ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- ተጫራቾች ከማንኛውም ሙስና እና የብከነት ድርጊቶች ነፃ ለመሆናቸው በፌዴራል እና በክልል የወጡትን የግዥ ደንቦች የሚያከብር ስለመሆኑ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምኖበት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን በሕገወጥ መንገድ እንዲካሄድ የሞከረ ከጨረታ ውጪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱም በሚካሄዱት ጨረታዎች እንዳይሳተፍ ተደርጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የሥራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0920762750 /0910285005/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
የመካከለኛ ኦሮሚያ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Summary
Gerbe Guracha Town Finance Office (Oromia) re-tenders its town corridor development works to construction contractors of grade G-3 and above with a renewed licence. Work experience and recommendation letters are preferred.
