በሲዳማ ክልል የአሮሬሳ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በመጆ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ ማውረጃ መንገድ ግንባታ ለማሰራት GC-5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን የጋበዘበት የጨረታ ማስታወቂያ።
በሲዳማ ክልል የአሮሬሳ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አሮሬሳ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት መጆ ከተማ በ2019 በጀት ዓመት ሊሰራ የታቀደው የኮብልስቶንና የጎርፍ ማውረጃ (cobblestone and drainage) መንገድ ሥራ ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ደረጃቸው GC-5 እና ከዛ በላይ የሆኑ ድርጅቶች 2019 በጀት ዓመት ፍቃዳቸው ያደሱና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN NO.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ አግባብነት ካለው የመንግሥት ተቋም (በፌዴራል እና በሲዳማ ክልል) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ( VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- አስፈላጊ የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
- በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀክት ሰርተው ለማስረከብ ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ መ/ቤት ወይም ከአማካሪ መ/ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም፡
- በገባው ውል መሰረት ፕሮጀክት ሰርቶ ያስረከበና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል።
- ድርጅቱ ለውድድር ያቀረበው ብቃት ( ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና ( ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳካሮ ትክክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ) የክፍያ ማዘዣ ( CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ (Bank gaurantiy) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያና ደንብ መሠረት ሕጋዊ ፍቃዳቸውንና ተ.ኢ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በአሮሬሳ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ ግዥ ሥራ ሂደት በመክፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይቱ በራሳቸው ወጪ አይቶ ማረጋገጥ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ ( CPO) ፋይናንሻል አንድ ዋና(ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ኮፒዎች ሰነድ በተለያዩ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት በአሮሬሳ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ ግዥ ሥራ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።
- ጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር ፐርሰንት(10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebeat) የተደረገ ከሆነ ድርጅቱ ቀጥታ ከጨረታ ወድድር ውጪ ይሆናል።
- አሠሪ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር - 0905090165
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት -0937186845/0923405050
በአሮሬሳ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት-0916368502
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አሮሬሳ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
Summary
Aroresa Woreda Urban and Infrastructure Office (Sidama) invites GC-5 and above contractors to build cobblestone roads with drainage in Mejo town. Bidders need a renewed licence, competence certificate, TIN, VAT and good past performance.
