በአርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ ዩኒየን ኃ/የተ የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴል 2014 ኢሱዙ FSR የጭነት መኪና (ሰሌዳ አአ-05-02431) በመነሻ ዋጋ ብር 8,000,000 ለመሸጥ ለስድስተኛ ጊዜ ያወጣው ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ።
አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ
ለስድስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያለዉን አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴል 2014 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ለጨረታው የወጣ ንብረትነቱ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት ሞዴል 2014 ንብረትነቱ የአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የሆነ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር አአ-05- 02431 የሊብሬ ቁጥር 401648 የሻንሲ ቁጥርJALK6A139E7102061 የሞተር ቁጥር 6HH1-473615 ሙሉ ሰፖንዳ ያለው ፤ መነሻ ዋጋ 8,000,000 (ስምንት ሚሊዮን ብር ) መሆኑን እንገልፃለን ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድሺ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ ቢሮ ሂጂ መሀመድ ባህሙድ መጋዘን መግር አካባቢ ባለዉ ግቢ ውስጥ መጥቶ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡
- ተጫራቾች ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል ከሆነ የዘመኑ የናሽናል ID (ዲጂታል መታወቂያ) እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያለውመሆኑን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ ፤ ድርጅት ከሆነ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር መከፈሉን የሚገልጽ መረጃ ከሚመለከተዉ አካል ማቅረብ አለበት እንዲሁም ሌሎች ተቁዋማት/ማህበራት ከሆኑ የተመዘገቡበትን ህጋዊ ሰርተፍኬት የዉክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለበቸዉ።
- ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውክልና ደብዳቤ እና የናሽናል ID ( ዲጂታል መታወቂያ) ማቅረብ አለበት ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጨረታው ለቀረቡት ንብረት 10% CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
- ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10:00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን መግር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ካለዉ ግቢ ውስጥ ኤፌሰር የጭነት መኪናውን ማየት ይችላሉ ።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ንብረት የዋጋ መቅረቢያ ቅጽ በመሙለት ቴክኒካል ዶክመንትና ፋይናንሻል ዶክመንት አንድ(1) ኦርጂናል እና አንድ(1) ኮፒ በተለያዩ ፖስታ አዘጋጅተዉ አንድ ላይ በማሸግ ሌሎች የተጠየቁትን መስፈርቶች በመጨመር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:30 (ሰዓት) ጀምሮ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ኃይል ተስፋዬ አሎፒክ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ተዘግቶ በ5:00 ሰዓት ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል።
- ጨረታው በ11ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 4:30(ሰዓት ) ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዳማ ከተማ መብራት ሀይል ተስፋዬ አሎፒክ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በዚሁ እለት በ5:00 (ሰዓት )ላይ በዚሁ ቦታ ይከፈታል።
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በሁለተኛ ቀን የግዢና ሽያጭ ውል ተፈራርሞ በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መውሰድ አለበት።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ከሽያጭ በኋላ ከስም ማዛወሪያ ጋር ተያይዞ ያሉትን ወጪዎች ከፍሎ ስሙ ወደ እራሱ ያዛውራል።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ አድራሻዉ ከላይ በተገለፀዉ በዩኒየኑ ቢሮ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0921096880/0920063165 ደውለው መረዳት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን። አድራሻችን፡- አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ 01 ቀበሌ መሆናችንን እንገልፃለን።
በአርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ
Summary
Arbagugu Farmers Cooperative Union (Arsi zone) sells a used 2014 Isuzu FSR cargo truck (Japanese make, plate AA-05-02431) by open tender, sixth announcement. The truck can be viewed at the union warehouse compound in Adama.
