Tender Detail

Tender Details

  • Company በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
  • Address በጋሞ ዞን አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-181-40-91
  • Website
  • Deadline02 Dec 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceበነፃ
  • Bid Securityየግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ 5% በCPO፣ Bid Bond ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበ8ኛዉ ቀን 8:00 ሰዓት
  • Sector Sales , Disposal Sale

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ያገለገሉ የመፀዳጃ ቤት ሲንኮች፣ የእጅ መታጠቢያዎች፣ የውሃ መያዣ ሲንኮች፣ የላሜራ ብረት በሮች፣ ታምቡራታ በሮችና የአሉሚኒየም የመስኮት ፍሬሞችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ያገለገሉ ዕቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የመፀዳጃ ቤት ሲንኮች ፣የእጅ መታጠቢያዎች ፣የዉሃ መያዣያ ሲንኮች የተለያየ ዓይነት የላሜራ ብረት በሮችና ታምቡራታ በር እና አሉሙኒየም የመስኮት ፍሬምና ፕ-ሽስ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታዉ መሳተፍና ዕቃዎችን መግዛት የሚፈልግ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት የስራ ቀናት ዉስጥ ወደ መ/ቤታችን ግዥና ንብረት አስተዳደር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነፃ መዉሰድ ይችላል።

ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ8ኛዉ ቀን ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። የ8ኛዉ ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል።

የጨረታ ማስከበሪያ የግዥዉን ጠቅላላ ዋጋ 5% ብር Cpo ; Bid Bond ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ።

ማሳሰቢያ፤ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከመሙላቱ አስቀድሞ የሚገዛዉን ዕቃ ባለበት ቀርበዉ ደረጃዉና ሁኔታዉን በሚገባ መመልከት አለበት።

አድራሻ ከዋናዉ ማዘጋጃ ከፍ ብለዉ ከመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዝቅ ብለዉ ወደ የትንበርሽ ማዞሪያ በዱንጉዛ ሕንፃችን ላይ እንገኛለን።
ስልክ 09-76-13-86-80

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

Summary
Arba Minch Zuria Woreda Finance and Plan Development Office (Gamo Zone) sells used items as-is: toilet and water sinks, hand basins, sheet-metal and tambourata doors, and aluminium window frames. Open to firms and individuals; bid documents are free.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender