የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በሻፋሞ ወረዳ ለዳዋሌ ባሎ (2.6 ኪ.ሜ) የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን አከራይ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ለመጀመሪያ ዙር ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር ሲ/መ/ባ/009/2019)።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ለመጀመርያ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር:- ሲ/መ/ባ/009/2019
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የፕሮጀክቱ ስም | በክልሉ ውስጥ የሚገኝበት ወረዳ | የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|---|---|---|---|
| 1 | ዳዋሌ ባሎ | ሻፋሞ | 2.6 |
በዚሁ መሠረት
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች መገልገያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር ከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም PPA List እና EGP portal ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውልታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ስራውን ያላጠናቀቀ ውሉ የተቋረጠበት የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
- አዲስ ፍቃድ ያለው አንድ ፕሮጀክት እና የሥራ ልምድ ያለው ሁለት ፕሮጀክት ብቻ መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር ) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁ -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ዋስትና (Unconditional Bid bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ የለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ገልባጭ መኪና እስከኮንዶር የስሪት አመን እ.ኢ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም 14ሜ.ኩ የሆነ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (Bid security)፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል )እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል )እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማዕተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣዩ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
- ባለስልጣኑ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር:- 0462-12-446
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
Summary
Sidama Roads Authority seeks owners to rent out dump trucks (2012 or newer, 14 m3) with loaders to haul gravel for the Dawale Balo road construction project (2.6 km) in Shafamo woreda. Licensed construction equipment rental firms with VAT, TIN, tax clearance and PPA/eGP registration may bid.
