የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የሚገኝ የቤ.ቁ 069 ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2019 ዓ.ም በድጋሚ በሐራጅ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አለምዝ ወርቁ እና የፍ/ባለዕዳ ጌታመሳይ ግርማ መከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 214677 ሴኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/274048 በ14/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የሚገኝ የቤ/ቁ 069 የሆነ ቤት በካርታ ቁጥር አ/13/46/7980/02 ሴሬ ቁጥር 031621 በአቶ ጌታመሳይ ግርማ ይመር ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ተነፃፃሪ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ቤቱ ያረፈበት 83 ካ.ሜ በፐሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ድርሻ ስፋት 60 ካ.ሜ ጠቅላላ በፐሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 143 ካ.ሜ አዋሳኞቹን በተመለከተ በሰሜን የመንግስት ቤት፣ በምስራቅ የመንግስት ቤት፣ በደቡብ አቶ ሰለሞን በምዕራብ አቶ ደስታ ቤቱ/ይዞታው አራት ኪሎ ቀበና ባለው የመንገድ የኮሪደር ፕላን ውስጥ ያረፈ በመሆኑ ለልማት የተያዘ መሆኑን የሆነው ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 7,391,918.00 (ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.274048 በቀን 10/02/2019ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,847,979.50 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ዘጠኝ ከ50/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 15 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጠም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
