የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባስኬቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞኑ የሚገኙ ያገለገሉ/የማይሰሩ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽኖች፣ ጀነሬተሮችና ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባስኬቶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ት ክልላዊ መንግሥት ባስኬቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞናችን የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ/የማይሰራ መኪናዎች ጀኔሬተሮችና ሞተር ሳይክሎች በሚገኙበት ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤
- ተሽከርካሪዎች /ጀነሬተሮች እና ሞተር ሳይክሎች የሚገኙበት አድራሻ ባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ዞን አስ/ር ጽ/ቤት ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ እና ላስካ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸዉን ከማቅረባቸው በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት በአካል በቦታው በመገኘት ከላይ በተገለጹት አድራሻ አስቀድመው ማየት እና ሲመለከቱ ከጨረታ ሰነድ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከአምስት የሥራ ቀናት በፊት ለፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ማሳወቅ አለባቸው። ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራቾች ጨረታው ከታሸገ በኋላ ለሚቀርበው አቤቱታ መ/ቤቱ ምንም ምላሽ ለመስጠት አይገደድም።
- ለተሽከርካሪዎች /ጀነሬተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ጨረታው ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የሚገዙትን የተሽከርካር /ጀነሬተሮች/ እና ሞተር ሳይክል በሚገዙበት የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) በደቡብ ኢ/ያ ክ/መ/ ባስኬቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ስም በማቅረብ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታው ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- የአሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ጀምሮ አምስት የሥራ ቀን በኋላ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች ሲፒኦ(cpo) ተመላሽ ይደረጋል።
- ስለአጫጫሪ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 09 የማይመለስ 1000 አንድ ሺህ ብር ብቻ/ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛዉም ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ ዋጋዉን በግልፅ በአሀዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለበት ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ /ማሽነሪ ንብረት ዋጋ በአንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ (cpo) የተጨመረበት ሁለት በፖስታ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 14/3/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22/3/2019ዓ.ም ዕለት ከቀኑ 6:30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በግልጽ የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች ዘግይቶ የደረሰ የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም ተጫራቾች በራሳቸዉ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉት ተሽከርካርና ማሽነሪ ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመክፈል ማንሳት አለባቸው፤ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት (CPO) ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ ይወጣል።
- መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ግልጽ ያደርጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0916720827 እና 0913988604 ይደውሉ: Tel:0462400237/38/39
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባስኬቶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Summary
Basketo Zone Finance and Plan Development Department (South Ethiopia) sells used and non-working vehicles, machinery, generators and motorcycles as-is in Laska town by open tender. Any Ethiopian individual or company may bid.
