ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለጎማ መልሶ መጠቀም ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የሚሆን 5,000 ባለ 11*20 እና/ወይም 12*20 ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ (ቁጥር 001/2019)።
ECWC RISING HONGFA PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለጎማ መልሶ መጠቀም ፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የሚሆን 11*20 እና/ወይም 12*20 የሆነ የተሽከርካሪ አሮጌ ባለሽቦ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | እቃ አይነት | መለኪያ | ብዛት | ጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ባለ11*20 እና/ወይም ባለ12*20 የተሽከርካሪ አሮጌ ባለሽቦ ጎማ | በቁጥር | 5,000 | 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ |
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ አግባብነት ያለው እና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በተለምዶ ውሃ ልማት ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው የኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃ/የተ/የግል ማህበር ዋና መ/ቤት GIW ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከታች የጨረታ መዝጊያ ተብሎ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከታች የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በግል ማህበሩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- የግል ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታው መዝጊያ ቀን:- ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሠዓት ጨረታው የሚከፈትበት ቀን:- ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:15 ሠዓት
አድራሻ ዋና መ/ቤት GIW ህንፃ 2ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር +251910614251
ኢኮስኮ ራይዚንግ ሆንግፋ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
Summary
ECWC Rising Hongfa PLC buys 5,000 used steel-wire vehicle tyres, size 11x20 and/or 12x20, as raw material for its tyre recycling plant. Suppliers with a renewed trade licence, VAT, TIN and tax clearance may bid.
