Tender Detail

Tender Details

  • Company አሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ
  • Address , Phone: 0911678567 /0930033441
  • Website
  • Deadline30 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

አሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ

አሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ


የጨረታ ማስታወቂያ

አሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ ያገለገለ የተሽከርካሪ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩ መስፈርቶች መሰረት ጨረታው ላይ እድትሳተፍ እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች

  1. ተጫራቾች ሕጋዊና የታደሰ የ2018/19 ዓ/ም ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ቢሆኑ ይመረጣል።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ወይም ዋጋ መቅረቢያ ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን ፊርማቸውንና ማህተም /የመታወቂያ ኮፒ/ አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ለጨረታ ሠነድ ከዋናው መስሪያ ቤት ጠመንጃ ያዥ ባንክ /ቴሌ ገራዥ/ ፊት ለፊት በሚገኘው የኋላ ወርቅ ህንፃ በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት በተዘጋጀው ዝርዝር ቅፅ ላይ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ 100% እና 15% ተ/እ/ታክስ ያካተተና፤ የሚያቀርቡትም ዋጋ በኢትዮጵያ ብር መሆን ይኖርበታል።
  6. ተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር ሁኔታ በአካል ለማየት ከፈለጉ በዋናው መ/ቤት በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዝ ፊት ለፊት ካለው ቢሮችን በሚገኘው የመኪና ማቆሚያ ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00- 10:00 ድረስ ማየት ትችላላችሁ።
  7. ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት በተዘጋጀው ዝርዝር ቅፅ ላይ ብቻ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
  8. አሸናፊው ተጫራች በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ማንሳት ይኖርበታል። በእነዚህ ቀን ውስጥ ባያነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል። ከአሸናፊነት ተሰርዞ ድርጅቱ የራሱን አዋጪ መንገድ በመጠቀም ዕቃዎቹን የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
  9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት ተጫራቾች ድርጅቱ ባዘጋጀነው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ዋና ሰነድ /Bid document/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀኑ 11:00 ድረስ በድርጅቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3:00 ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስ.ቁጥር-0911678567 /0930033441/ 0911393924

አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ

አሜዳድ ኃ/የተ/የግ/ማ

✨ messages.ai_summary
A PLC in Addis Ababa is selling various used vehicles as-is by open bid; vehicles can be inspected at its head office parking near Tele Garage, Bekelo Bet.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender