Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Bank S.C (ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ደንበል፣ ጌቱ ኮሜርሻል አጠገብ (ቦሌ ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት) ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115 572 098
  • Websitehttps://oromiabank.com/
  • Deadline18 Dec 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታው መነሻ ዋጋ 25% (CPO፣ በኦሮሚያ ባንክ ስም)
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ በነቀምቴና በአዲስ አበባ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ

Oromia Bank S.C (ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነትአበዳሪው ቅርንጫፍከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/ቀበሌየባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥርየቦታ ስፋት በካ.ሜ/ ሄክየጨረታ መነሻ ዋጋየጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታጨረታው የወጣው
1አቶ ጌታሁን ዱሬሳ ናዶተበዳሪውየመኖሪያ ቤትኩምሳ ሞሮዳኦሮሚያ ክልል፣ነቀምቴ ከተማ፣ጪለለቂ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 0310189/WLMN/2016323 ካ.ሜ4,206,556.96ታሕሳስ 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከ 4:00-5:00 ሰዓት ኦሮሚያ ባንክ ኩምሳ ሞሮዳ ቅርንጫፍ ውስጥ (ነቀምቴ ከተማ የሚገኝ)ለሁለተኛ ጊዜ
2አቶ ሁሴን አንድሬ ያሲንአቶ ሁሴን አሰፋው ሸበሽየመኖሪያ ቤትደሴአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 11AA000051105102267 ካ.ሜ16,459,114.31ታሕሣሥ 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከ 3:30-4:30 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤትለሶስተኛ ጊዜ
3አቶ አብርሃም መንግስቱተበዳሪውየመኖሪያ ቤት (G+3)ሀዊአዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 10 (አራብሳ ዳያስፖራ ሰፈር)LMK115154741150074444150 ካ.ሜ19,440,289.80ታሕሣሥ 09 ቀን 2019 ዓ.ም ከ 4:45-5:45 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤትለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
  2. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል። ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል።
  3. ተ.ቁ 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱ ንብረቶች ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ኦሎምፒያ አካባቢ አሜዳድ ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ የህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።
  4. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ሰዓት 5 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል። በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
  5. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል።
  6. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
  7. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር እና ማናቸውም ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል። ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
  8. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል።
  9. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 13 72 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት ወይም ለተራ.ቁ 1 በ 057-660-70 52 ኦሮሚያ ባንክ ኩምሳ ሞሮዳ ቅርንጫፍ፣ ለተ.ቁ 2 በ 033-312-00-31/64 ኦሮሚያ ባንክ ደሴ ቅርንጫፍ ፣ ለተ.ቁ 3በ 0114670663 ኦሮሚያ ባንክ ሀዊ ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
  11. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Oromia Bank S.C. is selling by open auction three residential houses held as loan collateral, in Nekemte town and in Yeka and Lemi Kura sub-cities of Addis Ababa.
Not stated in the notice: opening date, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender