የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በቁጥር ገጉወፋ/2270/18 በቀን በ15/07/2018 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዳቤ መነሻ ያገለገለ ተሽከርካሪ እና የተለያዩ ጋሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ 6/2019
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በቁጥር ገጉወፋ/2270/18 በቀን በ15/07/2018 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዳቤ መነሻ ያገለገለ ተሽከርካሪ እና የተለያዩ ጋሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ሎት 1:- ያገለገለ ሃዮንዳይ/HYUNDI/ የጭነት ተሽከርካሪ፣
ሎት 2:- የተለያዩ ጋሪዎችና ብረታ ብረቶች
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ:-
- ማንኛውም ይህንን ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ጨረታውን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለእያንዳንዱ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 6:00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታው ማስከበሪያ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም መሰራት አለበት።
- የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል።
- የተሽከርካሪው አይነት ሃዩንዳይ/HYUNDI/ የጭነት፣ ሞዴል 1M4፣ የተመረተበት ሀገር ኮሪያ፣ የተመረተበት አመት እ.ኤ.አ 2007 ሲሆን ተጫራቾች የተሽከርካሪውን ሁኔታ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጋሪዎችና የብረታ ብረቶች ሁኔታ ለመመልከት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ/የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ኦሪጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦሪጂናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 16ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።
ማሳሰቢያ:- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት።
* ከላይ የተገለፁ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸውም ግለሰቦች ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፣
ለበለጠ መረጃ 0113300112/0910027182
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ወልቂጤ
✨ messages.ai_summary
Gurage Zone Finance Department (Wolkite) is selling a used Hyundai truck (lot 1) and various carts and scrap metals (lot 2) by open bid; individuals without a trade licence may also bid.
