ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ ከ14 እስከ 16 ሰው የመጫን አቅም ያለውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Electric Vehicles) በዘርፉ ከተሰማሩት ድርጅቶች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/03/2019
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ ከ14 እስከ 16 ሰው የመጫን አቅም ያለውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Electric Vehicles) በዘርፉ ከተሰማሩት ድርጅቶች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታዉ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- በዘርፉ የተሰማሩ ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አስፈላጊዉን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ማንኛዉም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 በመምጣት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ማንኛዉም ተጫራች በገዛዉ የጨረታ ሰነድ ላይ ከብ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ።
- የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋዉን ዉል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ዉል መፈረም ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለዉም።
- ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ዉል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚዉል ሆኖ በ16ኛዉ ቀን በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዛዉ እለት 8:30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ።
አድራሻ :- ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19
ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ
Summary
Geda Transport and Logistics S.C. invites bids for the supply of electric passenger vehicles with 14 to 16 seat capacity. National open bid.
