Tender Detail

Tender Details

  • Company የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል
  • Address ኢትዯጵያ, Phone: 0465542060
  • Website
  • Deadline25 Nov 2026, 8:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityብር 30,000 (CPO)
  • opening dateበዚያው ዕለት ከቀኑ 5:00 ሰዓት
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Sales, Disposals And Foreclosure

የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል የአሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ

የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል


የአሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ
የጨረታ መለያ ቁጥር ዶ/ቦ/ገ/መ/አ/ሆ/01/19

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በከምባታ ዞን የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል በበጀት ዓመቱ ከሆስፒታሉ ውስጥ ረጅም ጊዜ ካገለገሉ ህክምና መገልገያ ማሽኖችና ህክምና ካልሆኑ ዕቃዎች የተከማቹ የተለያዩ አሮጊ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን (ብረታ ብረት፣ አልሙኒየም ብረቶች፣ ናስ ብረቶች፣ ኒኬል ብረቶችና መሰል ብረቶችን) በዘርፉ ፈቃድ ላላቸው ግለሰቦች ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪሎ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ነጋዴዎች /ግለሰቦች/ እነደሚከተለው ይጋብዛል፤

  1. በዘርፉ የተሰማሩ፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያሳቸዉና የመንግሥትን ግብር የከፈሉ፣
  2. የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN Number/ ያላቸው፣
  5. የተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ (CPO) በፖስታ በማሸግ ማስያዝ የሚችሉ፣
  6. የጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ቅጽ ከዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ከግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት በቁጥር #37 በአካል በመቅረብ ሰነዱን ወስደው ዋጋ መሙላት ይችላሉ።
  7. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት በከምባታ ዞን በዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር #37 በመቅረብ ዋጋ መሙላት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ የሞሉበትን ዶክሜንት በማሸግ በሆስፒታሉ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር #37 በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ በሆስፒታሉ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን በመክተት 4:30 ሰዓት ሳጥኑ ይታሸግና በዚያው ዕለት ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገጸበት ቀን አንስቶ ባሉት 3/ሦስት/ ቀናት ውስጥ ውል መግባት ይኖርባቸዋል። በውሉ መሰረት ባይቀርቡና ውል ባይፈጽሙ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው CPO ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ተጫራቹ በህግ ይጠየቃል።
  10. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
  11. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሳቢያ:- የጨረታ መከፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ ዕሁድና የበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ ሥራ ቀን ላይ የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0465542060/0465540763 ይደውሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በከምባታ ዞን የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Dr. Bogalech Gebre Memorial General Hospital (Kembata Zone, Central Ethiopia) is selling old scrap metals (iron, aluminium, brass, nickel) from long-used equipment by the kilo through open bid.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender