የሀዲያ ዞን የአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው ማዘጋጃ ቤት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ያወጣው ማስታወቂያ።
የአመካ ወ/ፋ/ጽ/ቤት ጌጃ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዲያ ዞን የአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳችን ለማዘጋጃ ቤት ኤሌክትሮኒክስ በጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- በመስመሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2019 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ
- ቫት እና የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ያላቸው ሆኖ የጨረታውን ሰነድ ከአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው 10 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ10ኛ ቀን 5:00 ሰዓት ታሽጎ በ5:05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን በጨረታው በተገለጸው መሰረት በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000/ አሥር ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይንም ካሽ ከጨረታ ሰነድ ጋር ይዞ መቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን የሚያካትት መሆኑ መገለጽ አለበት ታክስ በትክክል ካልተገለጸ የቀረበ ዋጋ ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል።
- የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን በፖስታ አሽጎዉ የድርጅቱን ስም ማህተምና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት።
- ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በኋላ ዘግይቶ የመጣ ኤንቨሎፕ ተቀባይነት አይኖርም እንደታሸገ ለተጫራቹ ይመለሳል።
- በጨረታ ለተሸነፉት ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ወይም ብር አሸናፊ ከተለየ በኋላ ይሰጣቸዋል።
- አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ ከሆነ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ አመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት አድርሰዉ ማስረከብ የሚችል።
- ባቀረቡት ዕቃዎች የጥራት ችግር ካጋጠመ በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል ካልቀየረ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል
- የአሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ወጭ እስከ አመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለማድረስ ፈቃደኛ የሚሆን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-93-42-04-60 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የአመካ ወ/ፋ/ጽ/ቤት
ጌጃ
Summary
Ameka Woreda Finance Office, Hadiya Zone, buys electronics for the woreda municipality through a tender. Bidders need a relevant trade licence renewed for 2019 E.C., VAT and taxpayer registration, and must deliver to the office at their own cost.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
