አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የሰራተኛች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ካፖርት፣ ቱታ፣ ሴፍቲ ጫማ ወዘተ…) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Africa Insurance Company (S.C.)
አፍሪካኢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ የተጫራቾች ማስታወቂያ
የጨረታቁጥር AIC; – 0017/2019
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የሰራተኛች የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ካፖርት፣ ቱታ፣ ሴፍቲ ጫማ ወዘተ…) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝይ ኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት የደንብ ልብሱን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠሲ ሲፒኦ (CPO) ኩባንያው ገቢ ያደርጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ገዝተው ለሚወዳደሩበት አይነት እና ብዛት የሚገልፅ የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በስራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች የቅድሚያ ክፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከፈለገ ከታወቀ ባንክ (Unconditional Guaranty) ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሊያስገቡ ሲመጡ የሚያቀርቡት የደንብ ልብስ ሳምፕል ኩባንያው በሚፈልገው ዓይነትና ጥራት መሠረት መሆን አለበት፡፡
- አንዱ ተጫራች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚታገድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የደንብ ልብሱን ከ2 ወር ባልበለጠ ጊዜ ወይም በውሉ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485 / 0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ
