የሲ/ብ/ክ /መ/ፐ/ሰ የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ለቢሮ ለስራ ጉዳይ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
የሲ/ብ/ክ /መ/ፐ/ሰ የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ለቢሮ ለስራ ጉዳይ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች
ሎት 2. የጽዳት እቃዎችን
በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት መሳተፍ ይችላሉ::
- በዘርፉ ሥራዎች የተሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ፡ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ /Tin numberያላቸዉ
- በገቢዎች ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለሎት1 10000/አስር ሽህ ብር ለሎት2 5000 አምስት ሽህ ብር በስፒኦ/CPO/ ወይም ቢድቦንድ የ60 ቀን ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ፡ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት::
- ተጫራች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበትቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር የሥራ ቀናት/ ዉስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሲ/ብ/ክ /መ/ፐ/ሰ የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ቀርቦ የንግድ ፍቃዳቸውን በማሳየት 100 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናል ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ሳጥኑም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11 /አስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4 :00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል::
- ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ ዋጋ የሚፀናበትን ከ45 ቀናት በታች የጊዜ ገደብ መስጠት የለበትም::
- ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ/ሂደት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል::
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እያንዳንዳቸዉን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በተፈለገዉ በተጠየቀው ስፔስፍኬሽን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኋላ ማስረከብ አለበት::
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት የስልክ ቁጥር 0939126096/0972743397 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ
ሀዋሳ
✨ messages.ai_summary
Sidama Region Public Service and Human Resource Development Bureau in Hawassa seeks suppliers of stationery (lot 1) and cleaning materials (lot 2). Open bid.
