Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት
  • Address ወላይታ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0465512100
  • Website
  • Deadline26 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 20,000 (CPO)
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከቀኑ 4:30
  • Categories Stationery Materials , Electronics Materials , Vehicle tire

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የጽ/መሣሪያ፣ የመኪና ጎማዎችን እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የጽ/መሣሪያ፣ የመኪና ጎማዎችን እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተለውን የመወዳደሪያ መስፈርት በማሟላት መወዳደር ይኖርባቸዋል:-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
  2. ግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ክፍያ ንብረት አስ/ር ደጋፊ የሥራ ሂደት እየመጡ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፣
  5. ተጫራቹ በባንክ የተረጋገጠ 20,000/ሃያ ሺህ ብር /ብቻ የያዘ C.P.O ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ከሠነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ለጨረታው መወዳደሪያ የሚቀርብ C.P.O በባንክ ማህተምና በባንክ ኃላፊ/ሠራተኞች ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት፣
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናልንና የኦርጅናል ኮፒ በፖስታ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ መጨረሻው ቀን ከቀኑ 11:00 ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው። የዕቃውን ጥራት በጥንቃቄ እናያለን፣
  7. ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አሥራ አምስት ቀናት/ ከቀኑ 11:00 ድረስ በሣጥኑ መጨመር አለባቸው። በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4:30 ሕጋዊ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥን ይከፈታል።
  8. ለጨረታው በዝርዝር ከተጠየቀው ዕቃ ዓይነት ውጪ ለመወዳደር ማቅረብ አይቻልም፣ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ በሕግ ተጠያቂ እናደርጋለን።
  9. በጨረታው ሠነድ የተፃፈውን የዕቃ ዓይነት ተጫራቾች በትክክል መሙላት አለባቸው፣ የሚያቀርቧቸው ዋጋ ከቫት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  10. ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብ ግደታ አለበት።
  11. ፍርድ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መለወጥ ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ በስልክ ቁጥር 0939834828 ወይም 0465512100 ደውለው መጠየቅ ይቻላል::

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Wolaita Zone High Court in South Ethiopia Region seeks suppliers of stationery, vehicle tyres and various electronics items for the 2019 budget year. Open bid.
Save Tender