Tender Detail

Tender Details


የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሀረጎ ኢንተርፕራይዝ የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የህንፃ መሣሪያ፣ የስፖርት ዕቃ፣ ደንብ ልብስና ጫማ ግዥ

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


ሀገር አቀፍ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ፤

ቁጥር:- ሐ/ኢ/ክ/ጨ3 -292/19ዓ.ም

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሀረጎ የማማከር የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃ ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ ፣ ሎት 5 የስፖርት ዕቃ ፣ ሎት 6 ደንብ ልብስ እና ሎት 7 ደንብ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
  3. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው::
  4. የግዥው መጠን ብር 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1- 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  6. ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸው እቃዎች በባለሙያ ማስፈ ተሸና ማረጋገጥ አለባቸው::
  7. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ::
  8. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት አለባቸው::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/በመክፈል በኢንተርፕራይዙ ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 002 ማግኘት ይችላሉ::
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 ብር 10,494(አስር ሺህ አራት መቶ ዘጠና አራት ብር ብቻ)፣ለሎት 2 ብር 2844(ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አራት ብር ብቻ)፣ለሎት 3 ብር 4800(አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር ብቻ)፣ ለሎት 4 ብር 2386(ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ብር ብቻ)፣ ለሎት 5 ብር 2403(ሁለት ሺህ አራት መቶ ሶስት ብር ብቻ)፣ለሎት 6 ብር 1871(አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አንድ ብር ብቻ)፣ሎት 7 ብር 1160 (አንድ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር ብቻ)በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከ73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ማስያዝ አለባቸው::
  11. ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት/በጥቅል/ ጠቅላላ ድምር ነው::
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ መም/ትም/ኮሌጅ ሀረጎ የማማከር የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ በግዥ፣ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 002 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከ03/03/2019 ዓ/ም እስከ 12/03/2019ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ::
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዝ በግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 02 በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል:: የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ላይ ይከፈታል::
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
  15. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠ/ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም ክፍት/ያልተሞላ/ እቃ ካለ ከውድድር ውጭ ያደርጋል::
  16. የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የተቀመጡ ሳምፕሎች ስላሉ ሳምፕሉን ይመልከቱ::
  17. ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ ፣የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ::
  18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሣሰቢያ:-

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሀረጎ የማማከር የምርምርና የንግድ ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Dessie College of Teacher Education Harego Consultancy, Research and Business Enterprise seeks suppliers in 7 lots: stationery, cleaning items, electronics, building materials, sports items, uniforms and uniform shoes. Open bid.
Save Tender