የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገግሎት መቐለ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያየ ዓይነት የፕሪንተር ቀለሞች እና የኮምፒውተር ወረቀት (A4 Computer paper) በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ (NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
Ethiopian Electric Utility (EEU) Mekelle REGION
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-MR/NCB/001/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገግሎት መቐለ ሪጅን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያየ ዓይነት የፕሪንተር ቀለሞች እና የኮምፒውተር ወረቀት (A4 Computer paper) በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ (NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
| ሎት | የዕቃው ዓይነት | ብዛት | የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰዓት |
| 1 | የተለያየ ዓይነት የፕሪንተር ቀለም (Tonner) | 462 | 50,000 | ህዳር 15/2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት | ህዳር 15/2019 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት |
| 2 | A4 ኮምፒውተር ወረቀት | 3,000 | 100,000 | ህዳር 15/2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት | ህዳር 15/2019 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ኪሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል::
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መቐለ ከተማ ሓወልቲ ክ/ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ ዛምራ ህንፃ የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 304 በመምጣት የማይመለስ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- አድራሻ:- መቐለ ከተማ ሓወልቲ ክ/ከተማ ፕላኔት ሆቴል ወረድ ብሎ በሚገኘው ዛምራ ህንፃ ላይ የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፅ/ቤት 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሳፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግት ቢሮ ቁጥር 304
- ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና << MEKELLE REGION ELECTRIC UTILITY >> በሚል መሆን ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል::
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የመቐለ ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Summary
Ethiopian Electric Utility Mekelle Region seeks suppliers of various printer toners and A4 computer paper in 2 lots. National open bid.
