ስኬት ባንክ አ.ማ የተለያየ መጠን ያላቸው የመኪና ተሽከርካሪ ጎማዎች ግዥ
Siket Bank S.C (ስኬት ባንክ አ.ማ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር SB/OT/NCB/11/04/2026
ስኬት ባንክ አ.ማ የተለያየ መጠን ያላቸውን የመኪና ተሽከርካሪ ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ወቅታዊ የሆነ የታክስ ክሊራንስ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸውን ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers List/ ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ / ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር /በመክፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የስራ ቀን በባንኩ ዋ/መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 407 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸኋል:: ጨረታው በዚሁ እለት በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈተው በሳይት ምልከታ/site visit ወቅት የሳምፕል ውጤታቸው ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ብቻ ይሆናል::
- ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኮፒ ሰነድ እና አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ ለየብቻው በማሸግ ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- ለጎማዎቹ ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል:: ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚመልሱበት ወቅት የሚያቀርቡትን ጎማ ብራንድ ባንኩ ባዘጋጀው የጎማ size መሰረት በግልጽ መጥቀስ የሚጠበቅባቸው ሲሆን በሳይት ምልከታ የሳምፕል ግምገማ በሚደረግበት ወቅት የጠቀሱትን የጎማ ብራንድ ባንኩ ባዘጋጀው የጎማ size መሰረት ማዘጋጀት አለባቸው:: በሳይት ምልከታ ወቅት ናሙና በጨረታ ሰነዱ ላይ የጠቀሰውን የጎማ ብራንድና የጎማ size ሳምፕል ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይደረጋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይ የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ቅጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል::
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ያልታሸገ ሰነድ፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያሰርዛል::
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ይመለስላቸዋል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፊርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታው መክፈቻው ቀን በስራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በሚውልበት ቀን እና ሰዓት መሰረት ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ሰዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል::
| ተ.ቁ | የሚገዛው የዕቃ ዓይነት | Cpo or unconditional bank guarantee |
| 1 | የተለያየ መጠን ያላቸውን የመኪና ተሽከርካሪ ጎማ | 300,000 |
የባንኩ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2:00 -11:00 ብቻ ነው::
አድራሻ:- ፒያሳ ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር: 011 1 27 55 85
ስኬት ባንክ አ.ማ
Summary
Siket Bank S.C. seeks suppliers of vehicle tyres of various sizes. Bidders must state tyre brands per the bank's sizes and present samples during a site visit; financial offers are opened only for those passing the sample check. Open bid.
