የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ ሸኔል ሆም የተገጣጣሚ ህንጻ ማምረቻ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በጥቅል 5ዐ/ሀምሳ/በግምት ሃያ አምስት ቶን የሚሆን 3 ሚሊ ሜትር ዲያ ሜትር ያለው ሽቦ በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፈ/ ከሳሽ -የአይለብሴ እና ደዋሮ የወል መሬት ተጠቃሚዎች እና በአፈ/ ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት-04-20741 የአፈፃፀም ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሆነ መኪና በግልፅ ጨረታ እንዲሸጥ አዟል።