የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፈ/ ከሳሽ -የአይለብሴ እና ደዋሮ የወል መሬት ተጠቃሚዎች እና በአፈ/ ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት-04-20741 የአፈፃፀም ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሆነ መኪና በግልፅ ጨረታ እንዲሸጥ አዟል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ ከሳሽ -የአይለብሴ እና ደዋሮ የወል መሬት ተጠቃሚዎች እና በአፈ/ ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ፣ የሰሌዳ ቁጥሩ ኢት-04-20741 የአፈፃፀም ተከሳሽ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የሆነ መኪና በግልፅ ጨረታ በመነሻ ዋጋ በብር 1,446,088 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ሰማኒያ ስምንት ብር/ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሐራጅ በጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት፤ የሽንብጥ ቀበሌ አስተዳደርአንድ ሰው ታዛቢ በመመደብ፣የአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የጨረታውን ስነ ስርዓት በአግባቡ አንዲከናወን ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ ፖሊስ በመመደብ፣ የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ሐራጅ ባዩ ጨረታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
በመሆኑም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ከቦታው ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መሳተፍ የሚችል አና አሸናፊው አንደታወቀም ያሸነፈበትን ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም 1/4ኛውን ማስያዝ የሚችል መሆኑን አንድታውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
