Tender Detail

Tender Details

  • Company ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address , Phone: 0911-33-72-66
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 20% (CPO)
  • opening dateሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት (CE) አንድ ያገለገለ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት (CE) አንድ ያገለገለ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. የመኪናውን ንብረት ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ ሲሆን፣ ተሽከርካሪው የሚገኝበት አድራሻ፡-
    - ሸገር ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ጉለሌ የገበያ ማዕከል ቅጥር ግቢ፣
  2. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የተሽከርካሪውን/ንብረት ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታወር አ/አበባ/ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በመገኘት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታወር አ/አበባ/ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ/ንብረት የመነሻ ዋጋ 20%(ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ(C.P.o.) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንለታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ በተናጠልና በግልጽ 15% VATን ማሳየት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታወር አዲስ አበባ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ/ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ቀናት በየቀኑ100.00(አንድ መቶ ብር) የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙትን ገንዘብ በቅጣት መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል፡፡
  8. ለጨረታ በቀረበው ተሽከርካሪ ንብረት ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈሉ ይሆናሉ፡፡
  9. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-33-72-66 እንዲሁም 0911-47-96-58 በመደወል ወይንም በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ኮድ-ኢትዮጵያ
አድራሻ፣ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት በሚገኘው ራህመት ታወር አ/አበባ/ ሕንፃ/ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306
ስልክ ቁጥር ፦ 0911-33-72-66 ወይም 0911-47-96-58

ኮድ-ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Code-Ethiopia Charity (CE) is selling one used vehicle by competitive bid. Bidders may inspect the vehicle at the Gulele market center compound and must submit a priced offer in a sealed envelope, with a 20% bid security in the form of a bank CPO.
Save Tender