በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ መስፈርቶችን (Specification) የሚያሟሉ ቢያንስ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2025 ሥሪት የሆኑ በቁጥር አስር Bajaj Boxer ሞተር ሣይክሎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 10 ወረዳዎች ለሚተገብረው የክትባት ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር ተዘጋጅተው ሥራ ላይ ከዋሉት ፎርማቶች መካከል የሕፃናት የዜሮ ዶዝ መመዝገቢያ መዝገብ እና የክትባት ታሊ ሽት መመዝገቢያ መዝገቦችን እያንዳንዳቸው በጥራዝ (በpad) ለማዘጋጀት ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት (Specification) መሠረት በሕትመት ሥራ ከተሰማሩ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።