በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 10 ወረዳዎች ለሚተገብረው የክትባት ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር ተዘጋጅተው ሥራ ላይ ከዋሉት ፎርማቶች መካከል የሕፃናት የዜሮ ዶዝ መመዝገቢያ መዝገብ እና የክትባት ታሊ ሽት መመዝገቢያ መዝገቦችን እያንዳንዳቸው በጥራዝ (በpad) ለማዘጋጀት ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት (Specification) መሠረት በሕትመት ሥራ ከተሰማሩ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ከርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጂንካ
የክትባት መመዝገቢያ ሕትመት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 10 ወረዳዎች ለሚተገብረው የክትባት ፕሮጀክት በጤና ሚኒስቴር ተዘጋጅተው ሥራ ላይ ከዋሉት ፎርማቶች መካከል የሕፃናት የዜሮ ዶዝ መመዝገቢያ መዝገብ እና የክትባት ታሊ ሽት መመዝገቢያ መዝገቦችን እያንዳንዳቸው በጥራዝ (በpad) ለማዘጋጀት ከዚህ በታች በተቀመጠው መስፈርት (Specification) መሠረት በሕትመት ሥራ ከተሰማሩ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
የሚዘጋጁት የሕትመት ሥራ መመዝገቢያ ጥራዞች /pads/ መስፈርቶች (Specifcation)
- Zero Dose (ZD) Immunization register pad (soft copy is ready by MOH and is available with our organization)
- Paper size: A4
- Number of Pages / pad - 200
- Inside page paper: 80 grams with black and white
- Cover page: 250 grams full color
- Number of pads to be printed - 560
- Zero Dose (ZD) Immunization tally sheet pad (soft copy is ready by MOH and is available with our organization)
- Paper size: A4
- Number of Pages/pad - 200
- Inside page paper: 80 grams with black and white
- Cover page: 250 grams full color
- Number of pads to be printed - 560
ስለሆነም ከላይ በተገለጸው መስፈርት መሠረት የሕትመት ሥራን መሥራት የሚችሉ እንዲሁም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የሕትመት ሥራ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ከዚህ በፊት የመንግስት ወይም ሌሎች ጥራቱን በጠበቀ ሕትመት ሥራን ሠርተው ማቅረብ የሚችሉ፣ ድርጅቶች ተመሳሳይ መመዝገቢያ መዝገቦችን በጥራት ጠርዞ የሚያውቁ ለዚህም ካቀረቡላቸው ድርጅቶች የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- ከላይ በተራቁ ከ1-3 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ አገልግሎት ሰጪ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በማስፈር በድርጅታቸው ማህተምና ፊርማ አረጋግጠው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ በሚገኘው የኮሚሽናችን የፕሮጀክት ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በአስረኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የኮሚሽኑ ሙያተኞችና የጨረታ ኮሚቴ፣ የክልል ጤና ቢሮ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ማለት ነው።
- ኮሚሽኑ በተጫራቾች የቀረበውን ጨረታ ሰነድ ላይ የሰፈሩትን የቴክኒክና የፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመ በኋላ የጨረታው አሸናፊ የሆነውን ድርጅት ያሳውቃል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በተነገረው በ 5 ቀናት ውስጥ ክክልሉ ጤና ቢሮ የተሰጠንን መመዝገቢያ መዝገቦች ሶፍት ኮፒ ከፕሮጀክት ጽ/ቤታችን መረከብ ይኖርበታል።
- የሕትመት ሥራዎች በትክክልና እና በተሰጠው መስፈርት መሠረት መሠራታቸውን አና በክልሉ ጤና ቢሮ፣ በኮሚሽናችን እና በፕሮጀክት ጽ/ቤት ባለሞያዎች ፍተሻ ካስደረገ በኋላ ጥራዝ መመዝገቢያ ፓዶችን ሕትመት ሥራ ያከናውናል። በሙያተኞች ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ በ10 ቀናት ውስጥ አጠናቅቆ ጂንካ ከተማ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ፓዶችን አጓጉዞ ማስረከብ ይጠበቅበታል።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን
