በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ መስፈርቶችን (Specification) የሚያሟሉ ቢያንስ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2025 ሥሪት የሆኑ በቁጥር አስር Bajaj Boxer ሞተር ሣይክሎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ከርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጂንካ
የሞተር ሣይክል የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ መስፈርቶችን (Specification) የሚያሟሉ ቢያንስ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን አቆጣጠር ከ2023 እስከ 2025 ሥሪት የሆኑ በቁጥር አስር Bajaj Boxer ሞተር ሣይክሎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሚፈለጉት የሞተር ሣይክሎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት
|
ተ.ቁ |
ዋና ዋና ክፍሎች (parts) |
መስፈርቶች (Specications) |
|
1 |
Engine |
¬ Type: 4 Stroke, Natural air cooled, SI engine ¬ Max Power: 12 PS @7500 rpm ¬ Max Torque: 12.55 Nm @ 5000 rpm ¬ Displacement: 144.8 cc ¬ Starting: Kick Start and Electric Start |
|
2 |
Brakes & Tyres |
¬ Break Size Front: 130 mm ¬ Brake Size Rear: 130 mm ¬ Tyre Front: 3.00 x 17, 45P ¬ Tyre Rear: 100/90 x 17,55P ¬ Brake Type Front: Mechanically Expanding Shoes, Drum ¬ Brake Type Rear: Mechanically Expanding Shoes, Drum |
|
3 |
Vehicle |
¬ Wheel Base: 1285 mm ¬ Length x Width x Height: 2016 mm x 740 mm x 1055 mm ¬ Suspension Front: 125 mm Fork travel, Telescopic ¬ Kerb Weight: 125 kg ¬ Fuel Tank (Reserve / Usable): 11 L ¬ Suspension Rear: 100 mm rear wheel travel, SNS |
|
4 |
Electricals |
¬ System: 12 Volts DC ¬ Battery: 12V 4Ah VRLA ¬ Head Lamps: 12V-35/35W-HS1 |
|
5 |
Accessories |
¬ Helmet ¬ Wind screen, and important accessories to the locality |
ስለሆነም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ Bajaj Boxer ሞተር ሣይክሎችን ማቅረብ የምትችሉ እንዲሁም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ከዚህ በፊት በሞተር ሣይክሎች አቅርቦት ላይ ሰርተው የሚያውቁ ለዚህም ካቀረቡላቸው ድርጅቶች የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የ2017/18 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቲኦቲ እና ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ከላይ በተራቁ ከ1-3 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ካሸነፈበት ቦታ እስከ ጂንካ (ፕሮጀክት ጽ/ቤት) ድረስ የማጓጓዣ ዋጋ ጨምሮ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በማስፈር በድርጅታቸው ማህተምና ፈርማ አረጋግጠው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ ከተማ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የ GAVE-RISE ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአስረኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ የኮሚሽኑ የጨረታ ኮሚቴ፣ የክልል ጤና ቢሮ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ኮሚሽኑ በተጫራቾች የቀረበውን ጨረታ ሰነድ ላይ የሰፈሩትን የቴክኒክና የፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመ በኋላ የጨረታው አሸናፊ የሆነውን ድርጅት ያሳውቃል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በተነገረው በ 5 ቀናት ውስጥ ትክክለኛነት እና በአግባቡ መስራታቸውን በኮሚሽናችንና በክልሉ ጤና ቢሮ ባለሞያዎች ፍተሻ ካስደረገ በኋላ ሞተር ሣይክሎችን በደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ ከተማ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልማትና ከርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የ GAVI-RISE ፕሮጀክት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ አጓጉዞ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- ድርጅቱ ለሚያቀርባቸው ሞተር ሣይክሎች ቢያነስ የአንድ ዓመት ዋስትና (warranty) መስጠት አለበት።
- ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የፕሮጀክት ጸ/ቤቱ አድራሻ፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን
የ GAVI-RISE ፕሮጀክት ጽ/ቤት
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ አሪ ዞን
ጂንካ ከተማ
አርኪሻ ቀበሌ ኬላ ሰፈር
ስልክ ቁጥር:- 09-16-18-40-84/09-16-16-30-95
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን
