በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው G+2 የከንቲባ ቢሮ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት ለተለያዩ ግንባታዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መጠን ያላቸው ፌሮ ብረቶችን ፣ ልሙጥ እና ሽብሽብ ፓርሊን ቆርቆሮዎችን ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፣ ሚስማሮችን እና ሲሚንቶ እንዲሁም ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ዴስክ ቶፕ ኮምፒተሮችን እና ላፕቶፕ ኮምፒተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡