Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-08-19-14-58
  • Website
  • Deadline18 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-06-18 00:00:00
  • Categories Building Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው G+2 የከንቲባ ቢሮ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለሚያስገነባው G+2 የከንቲባ ቢሮ ግንባታ በመስኩ የተሰማሩ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ደረጃቸው G.C-4/B.C3 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤

  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
  • የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ፤
  • የጨረታ ዋስትና 350,000 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤
  • የመስራት አቅም እንዳላቸው የሚገልፅ የወቅቱን የባንክ እስቴትመንት እና የስራ ልምድ ብቃት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  • የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልፅ የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ተቋራጮች ሰነዱን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ለሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ -

  • ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
  • የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጥም።
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 11 76 96 99 / 09 12 71 97 62 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በማዕ/ኢ/ክ/መ/በስልጤ ዞን የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender