አፈጻጸም ከሳሽ፡- ኢዮኤል ጌታቸው እና አፈጻጸም ተከሳሽ -ıኛ/ ታደለች ሃይሉ 2ኛ/ ዘነበች ሃይሉ 3ኛ/ ሰሳማዊት ሃይሉ መካከል ለላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፣ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በመርሳ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኘው ውሳኔ የተሰጠበት 6,872.62 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሆቴል (ድርጅት) ቤትና ቦታው በግል
የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ/ተከሳሽ የቆቦ ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን ኦርሶናይል ደናግል ገዳም ንብረት የሆነ በሰሜን የአፈጻጸም ተከሳሽ መዋዕለ ህጻናት እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በደቡብ የወንዶች ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን የገበያ ማእከል በምስራቅ መንገድ እና በምዕራብ የአፈጻጸም ተከሳሽ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ ክልል ውስጥ የሚገኝ 48 X 24 ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ግንባታው ያልተጠናቀቀ ህንጻ ያለ ምንም መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ በድጋሜ ትእዛዝ የሰጠ ስለሆነ በጨረታው ላይ ተሳታፊ መሆን የምትፈልጉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።