የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ/ተከሳሽ የቆቦ ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን ኦርሶናይል ደናግል ገዳም ንብረት የሆነ በሰሜን የአፈጻጸም ተከሳሽ መዋዕለ ህጻናት እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በደቡብ የወንዶች ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን የገበያ ማእከል በምስራቅ መንገድ እና በምዕራብ የአፈጻጸም ተከሳሽ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ ክልል ውስጥ የሚገኝ 48 X 24 ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ግንባታው ያልተጠናቀቀ ህንጻ ያለ ምንም መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ በድጋሜ ትእዛዝ የሰጠ ስለሆነ በጨረታው ላይ ተሳታፊ መሆን የምትፈልጉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት
በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈጻጸም ከሳሽ፡- ዝናቡ በዛ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና በአፈጻጸም ተከሳሽ፡- የቆቦ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ኦርሶናይል ደናግል ገዳም መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፡- የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደሴ ምድብ ችሎት መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት የአፈ/ተከሳሽ የቆቦ ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን ኦርሶናይል ደናግል ገዳም ንብረት የሆነ በሰሜን የአፈጻጸም ተከሳሽ መዋዕለ ህጻናት እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በደቡብ የወንዶች ካቶሊክ ቤተ ከርስቲያን የገበያ ማእከል በምስራቅ መንገድ እና በምዕራብ የአፈጻጸም ተከሳሽ መኖሪያ ቤት የሚያዋስኑት በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ ክልል ውስጥ የሚገኝ 48 X 24 ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ግንባታው ያልተጠናቀቀ ህንጻ ያለ ምንም መነሻ ዋጋ በጨረታ እንዲሸጥ በድጋሜ ትእዛዝ የሰጠ ስለሆነ እና ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ (ያቀረበ) አካል የጨረታው አሸናፊ የሚሆን በመሆኑ ማንኛውም መጫረት የሚፈልግ አካል ሚያዚያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ ህንጻው ከሚገኝበት ቦታ ላይ በመገኘት የግልጽ ጨረታ ተሳታፊ መሆን የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
-
- ጨረታው ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ጀምሮ 6፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል፡፡
- በጨረታው የሚሰተፍ ማኛውም አካል የታደሰ የቀበሌ መታወቂ ይዞ መገኘት አለበት፡፡
- ጨረታውን የሚያሸንፍ አካል ያሸነፈበትን የብር መጠን 1/4ኛ ወድያውኑ በባንክ ያስይዛል፡፡
የአብክመ ጠ/ፍ/ቤት ደሴ ቋሚ ምድብ ችሎት
