Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline01 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱ ግምት 1/4 (CPO)
  • opening dateኅዳር 22 ቀን 2019 ዓ/ም (ምዝገባ እንደተጠናቀቀ)
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የመኖሪያ ቤት ሐራጅ ሽያጭ (ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 08፣ 139 ካ/ሜ) - በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ዘውድነሽ እንዳለ እና የፍ/ባለዕዳ የሸዋጌጥ ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 22706 በ30/8/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/24770 በ17/10/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/24770 በ01/11/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር አዲስ ይዞታ መለያ ቁጥር AA000100804671 በእነ የሸዋጌጥ ታደሰ ደስታ (3 ሰዎች) ስም የተመዘገበ እና በሊዝ ስሪት የሚተዳደር የቦታ ስፋት 139 ካ/ሜ የሆነ ቤት ቤቱ ያረፈበት 43.34 ካ/ሜ የሆነ በግቢው ውስጥ ያለው ሌላ መኖሪያ ቤት ግድግዳ አንድ እና ያልተለየ ሲሆን ይዞታው 19.34ካ/ሜ መንገድ የሚነካው ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,090,190 (ሦስት ሚሊዮን ዘጠና ሺህ አንድ መቶ ዘጠና) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ኅዳር 22 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ¼ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ C.P.O የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Court-ordered auction of a residential house in Gulele Sub-city, Woreda 08, Addis Ababa: 139 sqm leasehold plot with a 43.34 sqm house, plus an adjoining undivided house sharing a wall. Bidders must deposit 25% of the estimate via CPO; the buyer pays transaction tax.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender