ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (አ.ማ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ከህጋዊ ንግድ ድርጅቶች/ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ (በምስረታ ላይ) አክሲዮን ለመሸጥ እንዲችል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወሰደው ፈቃድ መሰረት የአክሲዮን ሽያጭ በማከናወን ለምስረታ የሚሆነውን አክሲዮን ሽያጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል፡፡ በመሆኑም የአከሲዮን ሽያጭ የመጀመሪያው የጊዜ ገደብ እያበቃ በመሆኑ የምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረትና በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀጽ 261 መሰረት የምስረታ ኦዲት ሥራ ለማከናወን የሚችል የውጭ ኦዲተር መቅጠር ይፈልጋል፡፡