ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (አ.ማ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ከህጋዊ ንግድ ድርጅቶች/ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
ጨረታ ማስታወቂያ
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (አ.ማ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን እና በአካባቢው የሚገኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሲሆን በአሁኑ ወቅት በርካታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት (ቢሮዎችን) አደራጅቶ ሥራ ለመጀመር ዝግጅት እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡
በመሆኑም ዋና መ/ቤትን ጨምሮ ለተለያዩ ቢሮዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም Furniture (tables, chairs, shelves.), Equipment (computers, laptops, printers, photocopy machines....), Motor bikes, Published Materials (payment vouchers, receipt vouchers, journal vouchers, goods receipt vouchers), Supplies and Stationaries' ከህጋዊ ንግድ ድርጅቶች/ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርት፡-
• በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
• የአቅራቢነት ፈቃድ ያለው፤
• የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
• የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና
• የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
ተጫራቾች ተቋሙ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (አ.ማ) አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ከፍለው መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በዕለቱ ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ በአጭር ቀን ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ እጅ) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0978789522/0919363513/0916277582
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (አ.ማ)
