ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ (በምስረታ ላይ) አክሲዮን ለመሸጥ እንዲችል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወሰደው ፈቃድ መሰረት የአክሲዮን ሽያጭ በማከናወን ለምስረታ የሚሆነውን አክሲዮን ሽያጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል፡፡ በመሆኑም የአከሲዮን ሽያጭ የመጀመሪያው የጊዜ ገደብ እያበቃ በመሆኑ የምስረታ ቅድመ ዝግጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረትና በኢትዮጵያ የንግድ ህግ አንቀጽ 261 መሰረት የምስረታ ኦዲት ሥራ ለማከናወን የሚችል የውጭ ኦዲተር መቅጠር ይፈልጋል፡፡
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም የሚከተለውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች መጫረት ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
- ቻርተርድ/የተፈቀደለት የሂሳብ የኦዲት/ አዋቂነት ፈቃድ ያለው፣
- ከዚህ ቀደም በተለያዩ ተቋማት የሰራበትን መልካም ሥራ አፈፃጸም ውጤት የሚያመለክት ቢያንስ የሦስት ድርጅት በደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
ማሳሰቢያ:-
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋሞ ልማት ማኅበር ዋና ጽ/ቤት ግቢ ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም (በምስረታ ላይ) ማስተባበሪያ ፕሮጀክት የሥራ ክፍል /ጋሞ ባህል ማዕከል/ በቀለ ሞላ ሆቴል ጎን በመቅረብ የመወዳደሪያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ፣ በታሸገ ሰም ኤንቨሎፕ በዋጋ ማቅረቢያ ከአስፈላጊ ዶከመንቶች ጋር በማሟላት ከህዳር 1 እስከ ህዳር 10 ባሉት ተከታታይ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ሰዓት ድረስ ባለው ግዜ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ባይገኙም ሂደቱ አይስተጓጎልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርገው እንዲያመጡ እናሳስባለን፡፡
- አ/ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር ከፈለጉ 0916482815 ላይ ይደውሉ፡፡
ሰላም የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ