ደቦ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. ለ2026/27፣ 2027/28 እና 2028/29 የበጀት ዓመታት የተቋሙን የሒሳብ መዛግብትና የፋይናንስ ሪፖርቶች ኦዲት የሚያደርግ ብቁ የውጭ ኦዲት ተቋም በጨረታ ለመምረጥ ይፈልጋል::
Debo Micro finance Institution S.C (ደቦ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ)
ደቦ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ.
የውጭ ኦዲተር ለመምረጥ የጨረታ ማስታወቂያ
ደቦ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አ.ማ. ለ2026/27፣ 2027/28 እና 2028/29 የበጀት ዓመታት የተቋሙን የሒሳብ መዛግብትና የፋይናንስ ሪፖርቶች ኦዲት የሚያደርግ ብቁ የውጭ ኦዲት ተቋም በጨረታ ለመምረጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም ተቋሙ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን ማወዳደር ይፈልጋል::
- የተሳተፊ መስፈርቶች
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ምዝገባና TIN ማስረጃ::
- የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ::
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የተመዘገበበት የሙያ ፈቃድ::
- የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር MFI/37/2024 መስፈርቶችን ማሟላት::
- ቢያንስ የሦስት ዓመት የኦዲት ልምድ ያለው የቡድን ኃላፊ፣ በተለይም የፋይናንስ ተቋማት የኦዲት ልምድ::
- የIFRS ሥልጠና ማስረጃና በIFRS የተዘጋጁ የፋይናንስ ሪፖርቶች የኦዲት ልምድ::
- ከኦዲት ቦርዱ የዲሲፕሊን እርምጃ አለመኖሩን የሚገልጽ::
- የታጩ የኦዲት ቡድን አባላት የሕይወት ታሪክ (CV)::
- የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ
የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛሎችን ከሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ጋር በተለያዩ የታሸጉ ኤንቨሎፖች ውስጥ በማስገባት፣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: የጨረታውን ሰነድ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ 200 ብር ከፍለው መግዛት ይቻላል::
- ማሳሰቢያ
- የጨረታ ዋጋው የሦስቱንም የበጀት ዓመታት አገልግሎት ማካተት አለበት::
- ተቋሙ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ፦ 011 672 1518 / 19
አድራሻ፦ አዲስ አበባ, ቦሌ, ቲኬ ሕንፃ, 1ኛ ፎቅ, ቢሮ ቁጥር 111
✨ messages.ai_summary
Debo Micro Finance Institution S.C seeks a qualified external audit firm to audit its accounting records and financial reports for three consecutive budget years. Bidders must hold a renewed business license, VAT and TIN registration, tax payment proof, an accounting and auditing board professional license, National Bank Directive MFI/37/2024 compliance, a team leader with at least three years of audit experience (especially financial institutions), IFRS training and IFRS-based audit experience, no disciplinary action from the audit board, and team CVs.
Not stated in the notice: opening date, bid security. Check the original document or ask the issuer.
