Tender Detail

Tender Details

  • Company Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0251-12-49-28
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 8:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ኮድ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም
  • opening dateከ4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆነው በመጋዘን የሚገኙ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ጫማዎች፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣ የሞባይል ግላሶችና ከቨሮች፣ ስፔርፓርቶችና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2019 ባሉበት ሁኔታ ለመሸጥ ያወጣው ማስታወቂያ።

Dire Dawa Customs Branch Office (ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት)


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2019 በ 09/03/2019 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይ ግላሶች እና ከቨሮች፣ የእጅ ሰዓቶች ፣ ስፔርፓርቶች የአይታ ዕቃዎች/ መነፅሮች፣ መሬት ምንጣፍ፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የአስፖርት መሳሪያ መሳሪያዎች፣ የተለያዩ አርቴፊሻል ጌጣጌጥ ምግብ ነክ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአና ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ሙድአና ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነድ ለመግዛት ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአና ግቢ ነው።
  5. ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈሉ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
  6. ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  7. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት በእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
  8. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በለሰቱ ጠዋት በ2:00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ ከ4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፈለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  12. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 ( 0912885746)

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Customs Commission Dire Dawa Branch auctions confiscated goods as is: clothing, electronics, shoes, home and office items, phone accessories, watches, spare parts, cosmetics, construction, cleaning and sports items and more. Bidders need a sector licence, VAT and tax clearance.
Save Tender