የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ለመፈፀም ከተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ለመፈፀም ከተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፣
- ማንኛውም ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን እና የታክስ ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የውጪ አገር ተጫራቾች በሚሆኑበት ጊዜ በተቋቋሙበት አገር የተሰጣቸውን የኩባንያ ምዝገባ ወረቀት ወይም ፈቃድ ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን በድርጅታችን ፋይናንስ ዴስክ መውሰድ ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በTOR በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ዴስክ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ አዳራሽ ግራውንድ ፍሎር ይከፈታል።
- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ እንደተጫራቹ ምርጫ ለሎት 01 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሁለት ሺህ ብር)፣ ለሎት 02 የፅዳት እቃዎች ግዥ ብር 24,000.00 (ሃያ አራት ሺህ ብር)፣ ሎት 03 የመኪና መለዋወጫ ግዥ ብር 90,000.00 (ዘጠና ሺህ ብር) ለ3ቱም ሎት ለየብቻ የተሰራ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከህዳር 3 ቀን 2019 እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአከፋፈት ሂደት ባይገኙም የጨረታው የአከፋፈት ሂደት አያግደውም ።
አድራሻ:- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0115570640
አድራሻ ካዛንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ የስብሰባ አዳራሽ (ግራውንድ) ላይ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Defence Construction Design Enterprise buys in three lots by open tender: stationery, cleaning items and vehicle spare parts. Bidders need VAT, TIN, trade registration, tax clearance and a renewed sector licence; foreign bidders need company registration from their home country.
