በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Region Trade and Market Development Bureau (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና ንግድ ልማት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት:-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘረውን እያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው ፈርመውና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ ፋይናንሻል ኦሪጅናል አንድ ፎቶ ኮፒ እና ቴክኒካል ኦሪጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ለብቻ ለብቻ እና በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ግ/ን/ አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነዱን ንግድና ገበያ ልማት ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመምጣት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ሰነድ መሸጫ ዋጋ 500 (አምስት መቶ) ብር፣ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (cpo) ለኤሌክትሮኒክስ 30,000 (ሰላሳ ሺ) ብር ከቴክኒካል ኦሪጅናል ዶክመንት ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5:00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ወዲያውኑ ተጫራች(ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆ በሚቀጥለው የስራ ቀን 5:00 ሰዓት ታሽጎ 8:00 ሰአት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በተወዳደሩበት የዕቃ አይነት ያሸናፊነት ደብዳቤ እንዲደርሳቸው መስሪያ ቤት በመምጣት በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ጋራንቲ በማስያዝ ከቢሮው ጋር ውል መግባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ሲሞሉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ መሆን አለበት አለያ ውድቅ ይደረጋል።
- በጨረታ ላይ የወጡ ዕቃዎችን በሙሉ ኦሪጅናልና ጥራቱን የጠበቀ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነዱ መረዳት ይቻላል።
- ጨረታው አየር ላይ ጸንቶ የሚቆየው ለ 45 ቀናት ብቻ ነው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461459423/ 0461458944 ወይም 0912706505 /0913124044
አድራሻ:- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ቡታጅራ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Region Trade and Market Development Bureau (Butajira) buys various electronic items through an open tender. Bidders need a renewed sector trade licence, TIN, paid tax, VAT and supplier list registration; all items must be original and of good quality.
