Tender Detail

Tender Details


የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የጤና፣ የቢሮ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጥገናና አገልግሎት ግዥ ጨረታ (7 ሎቶች)

በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ግብአቶችን በጨረታ መግዛት ሎት1.የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ሎት2.የቢሮ ዕቃዎች ሎት3.ቋሚ ዕቃዎች ሎት4.ህትመቶች ሎት5.መድኃኒቶች፣ ሪኤጀንቶች እና የሕክምና እና የላቦራቶሪ እቃዎች ሎት6.የፅዳት ዕቃዎች ሎት7. ጥገና እና አገልግሎት (የኮምፒውተርና ፕሪንተር የላውንደሪ ማሽን የፎቶ ኮፒ ማሽን) እና የጀነሬተር ሰርቪስ እንዲሁም የጭነት አገልግሎት /ለአንድ አመት የሚቆይ/ በግልጽ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፋይ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የጨረታ ሰነዱ በሎት የማይመለስ ብር/200 ብር/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30-11:00 ሰዓት በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 413 መግዛት ይቻላል።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ በእያንዳንዱ ማለትም ለቢሮ ዕቃዎች፣ ለፅዳት ዕቃዎች ለቋሚ እቃዎች ለመድኃኒት ፤ ሪኤጀንት እና የሕክምና ዕቃዎች 3,500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጂናልና ኮፒውን ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በጤና ጣቢያው የግዢ ቢሮ ቁጥር 410 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው ዕቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ሲፒኦ (CPO) የሚያያዘው ኮፒው ላይ መሆን አለበት።
  8. አሸናፊው የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
  9. ኦርጅናል ፖስታዎችን በጨረታ መክፈቻ መወዳደር ወቅት የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
  10. የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ይሆናል።
  11. ጨረታው ለ10 የሥራ ቀን ክፍት በኋላ በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ዕለት ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  12. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቀ መሆን አለባቸው።

ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ መረጃ:- በቂርቆስ ክ/ከተማ ሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ ግዢ ክፍል ልዩ ቦታው ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሣርቤት በሚወስደው መንገድ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ አጠገብ በስልክ ቁጥር 0114706040 መደወል ይቻላል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Hiwot Amba Health Center, Kirkos Sub-City, Addis Ababa, buys in 7 lots by open tender: uniforms and sewing, office items, fixed items, printing, medicines and lab supplies, cleaning items, and a one-year equipment repair, generator service and transport contract. Licence and VAT needed.
Save Tender